የትምህርት ሚኒስቴር ፤ የአጠቃላይ ትምህርት የ2016 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደቱ የሚመራበት ሀገር አቀፍ የትምህርት ካላንደር ይፋ አድርጓል። በዚህም መሰረት ፤ ከመስረም 7 እስከ 11 ድረስ የትምህርት ሳምንት ሆኖ ይከበራል ብሏል። መስከረም 14 የአንደኛ ሴሚስተር መደበኛ የክፍል ውስጥ ትምህርት እንደሚጀምር አሳውቋል። በተመሳሳይ በዛው ዕለት የሬድዮ እና የቴሌቪዥን ትምህርት ስርጭት ይጀምራል።
የ1ኛ ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና ከጥር 27 እስከ የካቲት 1 እንደሚሰጥ የሚያሳየው የትምህርት ሚኒስቴር ካላንደር ከየካቲት 4 እስከ 8 ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ዝግ ሆነው የተማሪዎች ፈተና የሚታረምበት ውጤት የሚጠናቀርበትና የሚገለፅበት ወቅት እንደሆነ ገልጿል። የትምህርት ሚኒስቴር ካላንደር እንደሚያሳየው የካቲት 18 የሁለተኛ ሴሚስተር ትምህርት መደበኛ የክፍል ውስጥ ትምህርት የሚጀምር ሲሆን ከግንቦት 12 እስከ ግንቦት 23 የአጠቃላይ የትምህርት ማጠቃለያ (የ12ኛ ክፍል) ፈተና ይሰጣል።
ከግንቦት 26 እስከ 30 የ6ኛ ክፍል አንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ክልላዊ ፈተና ከሰኔ 3 እስከ 7 የ8ኛ ክፍል የመካከለኛ ደረጃ የማጠናቀቂያ ክልላዊ ፈተና ጊዜ እንደሚሆን ይፋ ተደርጓል። የሁለተኛ ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና ወቅትም ከሰኔ 17 እስከ 21 ሲሆን ከሰኔ 24 – 28 ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ዝግ ሆነው ፈተና የማረም፣ ውጤር የሚጠናቀርበት ፣ እና የሚገለፅበት እንደሚሆን ካሌንደሩ ያሳያል።
ሰኔ 30 ወላጆች እና የትምህርት ማህበረሰቡ በተገኙበት የአመቱ ትምህርት ማጠናቀቂያ ይሆናል።
* * ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ክልሎች በብሔራዊ ፈተናና በተለያዩ ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታዎች መነሻ የተወሰኑ የቀናት ለውጦች ሊያደርጉ እንደሚችሉ ታሳቢ እንደሚደረግ ማሳስቢያ ሰጥቷል።
Copyright © 2023. Luqman school